Tizita

ያ አሮጌ መጽሐፍ ተከድኖ የቆየ
ቀለማቱ አርጅቶ ደብዝዞ እየታየ
ተገልጦ ቢነበብ ንጉስ እንቅልፍ አጥቶ
ደግነት ቸርነት ተገኘበት ሞልቶ

የተረሳው ልቤ የአንተ ውለታ
ሲያስተውል ሲቃኘው በመንፈስ ትዝታ
ለካስ ተነግሮ የማያልቅ ተተርኮ ሌት ቀን
የማይወሳ ነው የአንተ ተዓምር

ባህሩን የከፈልክልኝ አዎ
ማዕበሉን አዘህ ጸጥ ያደረግከው
ትዝ እያለኝ አፌን ሞላው ምስጋና
ምህረትህ ደንቆኝ የአንተ ሥራ
ትዝ እያለኝ አፌን ሞላው ምስጋና
ቸርነትህ ደንቆኝ የአንተ ሥራ

ከወጥመዱ መሃል ስታስመልጠኝ
አልጥልህም አልተውህም እንዳልከኝ
አስታውሼ ውስጤን ሞላው ምስጋና
ምህረትህ ገርሞኝ የአንተ ሥራ
አስታውሼ ውስጤን ሞላው ምስጋና
ቸርነትህ ገርሞኝ የአንተ ሥራ

ኦ የአንተ ሥራ የአንተ ሥራ
ድንቅ ነው ግሩም ነው ድንቅ ነው ግሩም ነው

ሥራህ ግሩምና የኔ ጌታ ድንቅ ነው
ሥራህ ግሩምና የኔ የሱስ ድንቅ ነው

አንደበቴ ራደ አጣ የሚናገረው
ደርሰህ የታደግከው ያ ቀን ትውስ ቢለው
ልቤ ምቱን ሳተ ደስታ ፈንቅሎት
ያንተ መልካምነት በዝቶልኝ ምህረት
ከአይኖቼ ፈሰሰ የደስታዬ እንባ
ያወጣኸኝ ከሞትትዝታ እየመጣ

ድንቅ ነው ድንቅ ነው የኔ ጌታ ድንቅ ነው
ግሩም ነው ግሩም ነው የኔ የሱስ ድንቅ ነው

አንደበቴ ራደ አጣ የሚናገረው
ደርሰህ የታደግከው ያ ቀን ትውስ ቢለው
ልቤ ምቱን ሳተ ደስታ ፈንቅሎት
ያንተ መልካምነት በዝቶልኝ ምህረት
ከአይኖቼ ፈሰሰ የደስታዬ እንባ
ያወጣኸኝ ከሞትትዝታ እየመጣ

ባህሩን የከፈልክልኝ አዎ
ማዕበሉን አዘህ ጸጥ ያደረግከው
ትዝ እያለኝ አፌን ሞላው ምስጋና
ምህረትህ ደንቆኝ የአንተ ሥራ
ትዝ እያለኝ አፌን ሞላው ምስጋና
ቸርነትህ ደንቆኝ የአንተ ሥራ



Credits
Writer(s): Exodus Lambebo
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link