Brana (Intro)

እውነት፣ እውነት፣ ጀምበር ለአይን ውብ ናት
ልዳብስሽ ባይ የላት
ስቦ የሚገፋት
እኔስ ቀናሁባት (አሀ አሀ)

እርሶ ያከበሩት አላዋቂው እኔ (አሀ አሀ)
ለጥያቄዎት መልስ ቆምኩኝ የኔታዬ
አሃዱ ሚስጥር ነው ብዬ
ፍቅሬን ባከብር ጨከነች ገላዬ

አንቺው ዕጸ ለባዊት፣ አንቺው ውድቀት አዳም
ታምኜም እንዳልጾም ጎተትሽኝ ከገዳም

ምግባር አልባው ፍቅርም ቃል ብቻ ሆነብኝ
ንዴቴን ብከተል አክሊሌን ጣለብኝ

ደስታም ገጼን እንዳያውቅ አልኩት ና ዘመዴ
እርሱም ስቆ አለፈኝ ምንስ ናፍቆት ከኔ

ኧረ ጉድ ነው ላንቺስ፣
ሳቅሽን ብትስቂ እንባሽ ሆነኝ ቅኔ
ሳታውቂው ላወቅሽኝ ዕብነ ሐኪም እኔ



Credits
Writer(s): Mikiyas Mengistu Beyene
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link