Yeneta

አንድ አይደለም የሰማነው ሁለት ነበር ታሪኩ (ታሪኩ)
የመታዘዝ መስዋዕት ጆሮ ይሸለም ሰም እና ወርቁ

ጉልበት የሳመዉ ነበር ከእኛ አስተዋዩ
ለዓይን ትንሽ ግን ትልቅ አረገዉ ይህ ምግባሩ

ትልቁን ቀድጄ ትንሽ ከምሰፋ
ለአርምሞ እታጫለው በቃል ከምጠፋ
ሕይዎት ለመለዎጥ አንደበቴን ልግራ
ከባዶ ስንኜስ ዝምታ አላት ተስፋ

አሉ የኔታ ተረት ተረት
የመሰረት ተረት ተረት
የላም በረት
አንድ ምዕራፍ ነበር ይሄም ለልጅነት
አሉ የኔታ (ተረት ተረት)
አሉ የኔታ (ተረት ተረት)
አሉ የኔታ (ተረት ተረት)
የኔታ የኔታ (ተረት ተረት)

አዲስ ወግ ተላመድን
ባዶ ኪስ ሃጥያት ልክ እያረገን
ሰው ላይገባኝ ሰው ሆኜ
መፅዋች እጅም የለኝ እንደእምዬ፣ መልኬን ጥዬ

አሁን ለኔ ነጋ፣ ብራናዬን ላምጣ
ቅኔን እቀኛለው፣ ከእርሶ ተምሬያለው

ትልቁን ቀድጄ ትንሽ ከምሰፋ
ለአርምሞ እታጫለው በቃል ከምጠፋ
ሕይዎት ለመለዎጥ አንደበቴን ልግራ
ከባዶ ስንኜስ ዝምታ አላት ተስፋ

አሉ የኔታ ተረት ተረት
የመሰረት ተረት ተረት
የላም በረት
አንድ ምዕራፍ ነበር ይሄም ለልጅነት
አሉ የኔታ (ተረት ተረት፣ ተረት ተረት)
አሉ የኔታ (ተረት ተረት፣ ተረት ተረት)
(ተረት ተረት፣ ተረት ተረት)
የኔታ የኔታ (ተረት ተረት)



Credits
Writer(s): Mikiyas Mengistu Beyene
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link