Fetognalena

በባርነት በቀምበር ተይዞ
የተስፋው ሕዝብ በሃዘን ተውጦ
የሰቆቃ ጩኸቱን ሰማና
አሳረው ታደገውና
አቤት የእርሱ ሥራ

ነፃነቴን ቃሉ ነገረኝ
እኔን እመን ቀና በል አለኝ
ተፈትተሃል ምንድነው ጭንቀት
መጠራትህ ለነፃነት
አቤት የእርሱ ሥራ

ከላይ ወረደ ሕዝቡን ሊያሳርፍ በመስቀል ላይ ሞቶ
(ከላይ ወረደ ሕዝቡን ሊያሳርፍ በመስቀል ላይ ሞቶ)
የታሰሩትን ነፃ ሊያወጣ መፈታትን ይዞ
(የታሰሩትን ነፃ ሊያወጣ መፈታትን ይዞ)
ቀንበር ተሰብሯል አይዞህ አትፍራ ተረጋግተህ ኑር
(ቀንበር፡ ተሰብሯል አይዞህ አትፍራ ተረጋግተህ ኑር)
ተከፍቷል በሩ አምነህ ተራመድ አለኝ እግዚአብሔር
(ተከፍቷል፡ በሩ አምነህ ተራመድ አለኝ እግዚአብሔር)

(ፈቶኛልና) የኋላዬን አላይ
(ፈቶኛልና) የፊት የፊቴን እንጂ
(ፈቶኛልና) አዕምሮዬ ታድሷል
(ፈቶኛልና) ነፃነቴን፡ ላውጅ
(ፈቶኛልና) በፊቱ እዘላለሁ
(ፈቶኛልና) እንደተፈታ ሰው
(ፈቶኛልና) ጠላቴም ይፈር ይፈር
(ፈቶኛልና) የፈታኝ ኢየሱስ ነው

(ነፃ ላወጣን ለጌታ) ምሥጋና
(ነፃ ላወጣን ለጌታ) እልልታ
(ነፃ ላወጣን ለጌታ) ዘምሩ
(ነፃ ላወጣን ለጌታ) እልል በሉ

. (1) .

(ነፃ) ከሀጥያት (ነፃ) ከእስራት
(ነፃ) ከፍርሃት (ነፃ) ነፃ ነኝ

ይኸው እልልታ

የፈታኝ ነገረኝ ቀሰቀሰኝና
ቀንበርህ ተሰብሯል በል ሂድ ተነሳና
ተፈቶ ዝም የለም ይሰማል ምሥጋና
የዘመናት ታሪክ ተለውጧልና

ለፈታኝ (እኔ አለኝ ምሥጋና)
ላዳነኝ (እኔ አለኝ ምሥጋና)
ለጌታ (እኔ አለኝ ምሥጋና)
ለኢየሱሴ (እኔ አለኝ ምሥጋና)

ይኸው እልልታ



Credits
Writer(s): Simone Tsegay
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link