Medehanialem

"ስብሐተ-እግዚአብሔር ይነግር አፉየ ኩሉ ዘስጋ ይባርክ
ለሥሙ ቅዱስ ለዓለም ወለዓለመ-ዓለም"

አሜን ሀሌሉያ እያሉ
ቅዱስ አለ እርሱ ዘምሩ
ዛሬም እርሱን የምትፈሩ
አምላካችሁን አመስግኑ

ከድንግል ማርያም ከብፅህት ተወልዶ
ወደ ምድር መጣ ዓለምን ሁሉ ወዶ
በመስቀሉ ስራ ሁሉን ሊያስታርቅ
የባርያን መልክ ይዞ ወረደ ያለም መድሐኒት

የድሃደግ አባት የመበለት ዳኛ
እራሱን አዋርዶ ሞተልን ስለኛ
የሞትን ጣር ሁሉ አጥፍቶ ተነሳ
የጥሉ ግድግዳ ፈረሰ ሲዖልን ድል ነሳ

ተስፋ የለኝ ብሎ ውስጡ ባዘነዉ
ሰው ለማይረዳው ልቡን ሚያልበዉ
እንባውን አብሰህ አቅፈህ ምታጽናና
ክብርና ሞገስ ይብዛልህ ምሥጋና

በአብ ቀኝ ያለው (መድኃኒያለም)
ስለ እኛ የሞተው (መድኃኒያለም)
ከሞት የተነሳው (መድኃኒያለም)
በክብር ያረገው አዬ (መድኃኒያለም)
በዙፋኑ ያለው (መድኃኒያለም)
ደግሞም የሚመጣው አዬ (መድኃኒያለም)

እግዚአብሔርን አመስግኑ
ቸርነቱን ተናገሩ (ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም)
ሰማያትን ሰራ (ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም)
ምድርን ዘረጋ (ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም)
መላዕክት ሰገዱ (ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም)
ይገባዋል አሉ (ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም)

ኧኸ ኧኸ

ይገባዋል ይገባዋል
ይገባዋል ይገባዋል (ታርዷልና)

በከበሮ (አመስግኑት)
በመሰንቆ (አመስግኑት)
በበገና (አመስግኑት)
በዕልልታ (አመስግኑት)

ኧኸ ኧኸ

ይገባዋል ይገባዋል
ይገባዋል ይገባዋል (ታርዷልና)



Credits
Writer(s): Simone Tsegay
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link