Yene Nesh

- የኔ ነሽ

ሚኪ ጃኖ ኧሃ ሃ ሃ ሃ ሃ ሃ
ቴዲ ዮ
ያሳደገኝ ለምለም ሀገር
በ የኔታ በቂስ መንደር
ቅኔ ደጓ ፊደል መቁጠር
የልጅነት ልምዴ ነበር
የምናይ ፍሬ ያይበገር
የአትንኩኝ ባይ የፋኖ ዘር
ያ ገበሬ ያ ገራገር
የእሱ ልጅ ነኝ የባላገር
አብሮ አደግ ጓደኛዬ
መጣሁኝ አንቺን ብዬ
የልጅነት ትዝታዬ
መለሺኝ ከቀዬ
በአመትባል በአል ደመራ
ችቦ ሰርተን ስናበራ
በእልልታ ደምቆ ዳንኪራ
አፍ ለአፍ ገጥመን ስናወራ
አስታወሺኝ ልጅነቴን
ባንድ ማዕድ ጎረቤቴን
አረሳም የእናት አባቴን
የባላገሩ ደሀ ቤቴን
የኔ ነሽ የኔ ነሽ ውዴ የኔ ነሽ
የኔ ነሽ የኔ ነሽ ውዴ የኔ ነሽ
የኔ ነሽ የኔ ነሽ ውዴ የኔ ነሽ
የኔ ነሽ የኔ ነሽ የኔ ነ. . . ሽ
የኔ ነሽ የኔ ነሽ ውዴ የኔ ነሽ
የኔ ነሽ የኔ ነሽ ውዴ የኔ ነሽ
የኔ ነሽ የኔ ነሽ ውዴ የኔ ነሽ
የኔ ነሽ የኔ ነሽ የኔ ነ. . . ሽ
የዘምዘም እናት ጎረቤታችን
እትዬ አስካል አበ ልጃችን
ለድግስ መተው ዘመዶቻችን
ተረሳሽ ወይ ጨዋታችን
እሸት ባቄላ ከማሳ ቀጥፈን
ወዲያው ተጣልተን
ወዲያው ታርቀን
ሾላ ለማውረድ ከዛፍ ስንወጣ
መሬት ቆፍረን ጉርጓድ ገበጣ
ጊዜው ቢረዝም ከሀገር ብንወጣ
የህል ውሀ ነገር መልሶ አመጣ
ቆቃ ቦራ ጥጃው ሺ መክት
ሰንጋ ፈረስ የሺ ሰው ግምት
የገብስ ቆሎ የዘገንበት
ታናሽ ታላቅ የቆረጥንበት
ወገል ማረሻ እርፍና ድግሩን
ጠምደን ወተን ሞፈር ቀንበሩን
አርብ በጁማ እሁድ በሰንበት
ከርሻ ከአጨዳ እምናርፍበት
ተረሳሽ ወይ ምንዝናናበት
ደጉ ዘመን የቦረቅንበት
የኔ ነሽ የኔ ነሽ ውዴ የኔ ነሽ
የኔ ነሽ የኔ ነሽ ውዴ የኔ ነሽ
የኔ ነሽ የኔ ነሽ ውዴ የኔ ነሽ
የኔ ነሽ የኔ ነሽ የኔ ነ. . . ሽ
እሷ ጨዋ ናት ቤተሰብ አክባሪ
ተገዢ ለፈጣሪ
ያገሬ ውዷ ተፈቃሪ
ኮኮብ ናት ተወርዋሪ
ደስታዬ ሞላ ስሆን ካንቺጋ
ምሽቱም ባንቺ ነጋ
እኔ አልፈልግም ከንግዲ አልሰጋ
አንቺን ሰጥቶኛል ፀጋ
የኔ ነሽ የኔ የኔ የኔ
ዜማዬ ነሽ ቅኔ ቅኔ ቅኔ
አልጣሽ ካይኔ ካይኔ ካይኔ
ላድርግሽ ሁሌ ጎኔ ገኔ
በልቤ ትርታ የተፈቀርሽ
በጎድኔ ስር የተፈራገጥሽ
ህይወቴ ሙሉ ስጠብቅሽ
መልሶ አመጣኝ ጨዋነትሽ
ጎጆ ጥላዬ ማዕድሽ ወጉ
ልቤ ዝምድናው ሳር ምርጉ
ባለሞያ ነሽ ጎበዝ ትጉ
ልወስድሽ መጣሁ እንደ ወጉ
(የኔ ነሽ የኔ ነሽ ውዴ የኔ ነሽ)
የኔ ነሽ የኔ ነሽ ውዴ የኔ ነሽ
የኔ ነሽ የኔ ነሽ ውዴ የኔ ነሽ
የኔ ነሽ የኔ ነሽ ውዴ የኔ ነሽ
የኔ ነሽ የኔ ነሽ የኔ ነ. . . ሽ
የኔ ነሽ የኔ ነሽ ውዴ የኔ ነሽ
የኔ ነሽ የኔ ነሽ ውዴ የኔ ነሽ
የኔ ነሽ የኔ ነሽ ውዴ የኔ ነሽ
የኔ ነሽ የኔ ነሽ የኔ ነ. . . ሽ



Credits
Writer(s): Solomon Ambaw
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link