Atsedeken

ክብር ምስጋና ይሁን ለእግዚአብሔር
ወዶናልና ከቶ ላይተወን በዘላለም ፍቅር
ክብር ምስጋና ይሁን ለእግዚአብሔር
በራሱ ምሏል ከቶ ላይተወን ታላቅ ርስቱ ነን
ኦሆሆሆ
ወድቀን ሳለን ተጥለን ስንጨነቅ ሚረዳን አጥተን
በደም ተለውሰን ሳለን በብዙ ስቃይ ተስፋ ቆርጠን
አይቶ እጅግ ራራልን ቁስላችንን አጥቦ ፈወሰን
ልጁን በወደደበት ፍቅር እኛንም እንዲሁ ወደደን

አዳነን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ ጠራን
የእሱን ፍቅር በጎነት እንድንናገር ተመረጥን
ታላቅ ሕዝብ አደረገን የተለየ የንጉሥ ካህን
ምህረትን አግኝተን ተባልን የእግዚአብሔር ወገን

(ወገን ወገን ወገን) ወገን አደረገን
ልጆች ልጆች ልጆችልጆቹ አረገን

አምላክ ተብሎ ሊጠራብን እግዚአብሔር ስላላፈረብን
ከእሱ ጋር አብረን እንድንኖር በሰማይ ስፍራ አዘጋጀልን
ወደደን ደግሞም አጸደቀን ከእንግዲህ ማነው ሚኮንነን
ሰጥቶናል የልጅነት መንፈስ እንድንጠራው አብ አባት ብለን

አዳነን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ ጠራን
የእሱን ፍቅር በጎነት እንድንናገር ተመረጥን
ታላቅ ሕዝብ አደረገን የተለየ የንጉሥ ካህን
ምህረትን አግኝተን ተባልን የእግዚአብሔር ወገን

(ወገን ወገን ወገን ወገን አደረገን)
ልጆቹ አረገን አጸደቀን
በክርስቶስ ወደደን የራሱ አረገን
አጸደቀን



Credits
Writer(s): Samuel Alemu, Dawit Getachew
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link