Oh Nefse

ነፍሴ ሆይ አስቢው ያደረገልሽን እግዚአብሔር
ከጥፋት ከልሎ እዚህ ያደረሰሽን ሆኖሽ ቅጥር
ከደዌሽ በሙሉ የፈወሰሽ
በጭንቅ ሰዓት የደረሰልሽ

ጎልማሳነትሽን እንደ ንሥር ጉልበት የሚያድሰው
ምኞትሽን ከበጎ ነገር የሚያረካ እግዚአብሔር ነው
ሕይወትሽን ያዳነ ከጥፋት መንገድ
ከፊት ለፊትሽ ቀድሞ ሚሄድ
ህያው ሰውነቴ ቅዱስ ነው
በቀንም በማታ አክብሩት እሱን
እግዚአብሔር መሀሪ ይቅር ባይ ነውና
ነፍሴ ሆይ እያሰብሽ አቅርቢ ምስጋና

ኦ ነፍሴ እባክሽ
ምህረቱን እያሰብሽ አመስግኚው
ርህራሄው እጅግ ብዙ ነው
ኦ ነፍሴ እባክሽ
ፍቅሩን እያሰብሽ አመስግኚው
ርህራሄው እጅግ ብዙ ነው

ለቁጣው የዘገየ ፍቅሩም የበዛ አምላክ ነውና
ለሚጠሩት ሁሉ የምህረት አምላክ ነው የእንደገና
ምስራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ መጠን
ከአንቺ አስወገደው ሚያስጨንቅሽን
እንደሚራራ አባት ለውድ ልጆቹ
ዘወትር የያዘሽ በሰፊው እጆቹ
ነፍሴ ሆይ አስቢ ታላቅ ውለታውን
ሁልጊዜ አፍልቂ ለሱ የሚገባውን

ኦ ነፍሴ እባክሽ
ምህረቱን እያሰብሽ አመስግኚው
ርህራሄው እጅግ ብዙ ነው
ኦ ነፍሴ እባክሽ
ፍቅሩን እያሰብሽ አመስግኚው
ርህራሄው እጅግ ብዙ ነው

በበረሃው ምድር ምንም በሌለበት
ለጥምሽ እርካታ ለድካምሽ እረፍት
ከጠላት ፍላፃ ከቀስተኛው ትኩረት
ከለላ የሆነልሽ ከአንቺ ፍቅር ይዞት
በለመለመው መስክ ዘውትር እየመራ
በጠላትሽም ፊት በዘይት የቀባሽ
እንደበደልሽ ያልከፈለሽ
ምህረቱን ያበዛልሽ ፡ እግዚአብሔር ነው

ኦ ነፍሴ እግዚአብሔር ባርኪ
ኦ ነፍሴ እግዚአብሔር ባርኪ



Credits
Writer(s): Samuel Alemu, Dawit Getachew
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link