Tsegaw Bemnet Adinonal

ሰውን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ፀጋ በክርስቶስ በኩል ተገልጧል
ለሚያምን ሁሉ የሀጢያት ስርየት እንዲሁ በነፃ ያደርጋል
ተስፋ ለቆረጡ ለተጨነቁ በሞት ጥላ ውስጥ ላሉ ሁሉ
ወደ ህይወት መንገድ ይመራቸዋል ጉልበት አለው ደሙ

ፀጋው በእምነት አድኖናል
ክርሰቶስ ቤዛ ሆኖልናል
ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ እንጂ ከእኛ ስላይደለ
ከቶ እንደለፋንበት አንመካም

አንመካም

ቅን ፈራጅ ጻድቅ አምላክ ነውና እንከን የሌለበት
ሀጢያተኛውን ሊያጸድቅ ወዶ ልጁን አደረገው ሀጢያት
እውነትን እና ምህረትን አስማምቶ እኛን አጸደቀን
በክርስቶስ በኩል በነፃ የተሰጠን የፀጋው ክብር ይመስገን

ፀጋው በእምነት አድኖናል
ክርሰቶስ ቤዛ ሆኖልናል
ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ እንጂ ከእኛ ስላይደለ
ከቶ እንደለፋንበት አንመካም

ስለሚገባን ሳይሆን እንዲሁ ስለወደደን
ከዘላለም ሞት ሊያድነን ፀጋውን ላከልን
እያስተማረ እየረዳ እስከ ፍፃሜው ሊያደርሰን
እግዚአብሔርን እንድንመስል ፀጋው ነው ሚረዳን

በፀጋው ላዳነን
ለኢየሱስ ክብር ይሁን
ይገባዋልና ክብርና ምስጋና አሜን
ለፀጋው ክብር ይሁን
ላዳነን ክብር ይሁን
ለኢየሱስ ክብር ይሁን
አድኖናልና እንዲሁ በፀጋ አሜን



Credits
Writer(s): Samuel Alemu, Dawit Getachew
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link