Tilik Neh

ደማቁ ብርሃን በአንተ ይሰወራል
ህያው ማንነትህ ከዘላለም ያልፋል
አቤት የአንተ ውበት ሞገስህ ሲያበራ
አትወዳደርም ከሰራኸው ጋራ

ትልቅ ነህ ከምንልህ በላይ
ከገባህን በላይ ከሰበክንህ በላይ
ኀያል ነህ ብለን ካልንህ በላይ
ከዘመርንህ በላይ እግዚአብሔር ሆይ

ለግዛትህ ወሰን ፋፃሜ የለውም
በእጅህ ላይ ናቸው ዛሬና ዘላለም
ከጊዜ ውጭ ያለህ በጊዜ ምትሰራ
ዙፋንህ የፀና የለ የሚያስፈራህ

ትልቅ ነህ ከምንልህ በላይ
ከገባህን በላይ ከሰበክንህ በላይ
ኀያል ነህ ብለን ካልንህ በላይ
ከዘመርንህ በላይ እግዚአብሔር ሆይ

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ያለና የነበርክ
ለዘላለም የምትኖር በግርማህ
ሰማይና ምድር በክብርህ ተሞልቷል
እግዚአብሔር አንተን ከቶ ማን ይመስላል

አንተ ልዩ ነህ አንተ ልዩ ነህ
ልዩ ነህ አንተ ልዩ ነህ

ትልቅ ነህ ከምንልህ በላይ
ከገባህን በላይ ከሰበክንህ በላይ
ኀያል ነህ ብለን ካልንህ በላይ
ከዘመርንህ በላይ እግዚአብሔር ሆይ



Credits
Writer(s): Samuel Alemu, Dawit Getachew
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link