Amnihalehu

ሁሉን የምትችል የአብርሃም አምላክ
ስለ ተስፋ ቃልህ ቅዱስ ስምህ ይባረክ
በእምነት በመጽናት ክብርን እሰጥሀለው
አልጠራጠርም ቃልህን አምናለው

እግዚአብሔር ሆይ እኔ አምንሀለው
ከማየው በላይ ቃልህን አምናለው
በምንም አይነት እንደማተወኝ
የከፈልክብኝ ኢየሱስ አሳየኝ
እግዚአብሔር ሆይ እኔ አምንሀለው
ከራሴ በላይ ቃልህን አምናለው
በዙፋንህ ላይ የምትኖር ፀንተህ
ለሚወዱህም ዋጋን እየሰጠህ

ከጠየኩህና ከማስበው በላይ
ማድረግ ለሚቻልህ ያለ አንዳች ከልካይ
ተስፋን በሚያስቆርጥ ባለቀ ነገር ላይ
ህይወት የምትዘራ አንተ አይደለህም ወይ

እግዚአብሔር ሆይ እኔ አምንሀለው
ከማየው በላይ ቃልህን አምናለው
በምንም አይነት እንደማተወኝ
የከፈልክብኝ ኢየሱስ አሳየኝ
እግዚአብሔር ሆይ እኔ አምንሀለው
ከራሴ በላይ ቃልህን ይዣለው
በዙፋንህ ላይ የምትኖር ፀንተህ
ለሚወዱህም ዋጋን እየሰጠህ

በእምነት እጠብቃለሁ ቃልህን በተስፋ
የሚታይ ደመና ለጊዜው ቢጠፋ
ኃይሌ አንተ ነህና ፍፁም አልታክትም
በአንተ የታመኑትን ከቶ አትጥላቸውም

ክንድህን ታምኜ በአንተ እመካለው
የነገርከኝን ተስፋ አደርጋለው
በቃልህ ታማኝ አምላክ ነህና
እጠብቅሃለው ሆኜ በምስጋና
ክንድህን ታምኜ በአንተ እመካለው
የነገርከኝን ተስፋ አደርጋለው
በቃልህ ታማኝ አምላክ ነህና
እጠብቅሃለው ሆኜ በምስጋና
ክንድህን ታምኜ በአንተ እመካለው
የነገርከኝን ተስፋ አደርጋለው
በቃልህ ታማኝ አምላክ ነህና
እጠብቅሃለው ...



Credits
Writer(s): Samuel Alemu, Dawit Getachew
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link