Teneka

የፍቅርሽ ጉልበት ሲለካ
በምንም አይተካ
ልቤ ከንቱ ሲመካ
ጥሎታል ፍቅርሽ ለካ
ልቤ ሲመዘን ሲለካ
በፍቅርሽ ወድቋል ለካ
ማመን እንጂ ሲነቃ
መሸፋፈኑ በቃ
ታወቀብኝ ተነቃ ተነቃ
ያላንቺ አልኖርም በቃ
ታወቀብኝ ተነቃ ተነቃ
ያላንቺ አልኖርም በቃ
አልረታም እያልኩ ስኩራራ ስመካ
ዉስጥ ዉስጡን ተይዤ ታስሪያለዉ ለካ
ለአንድ ጀንበር ሳጣሽ የጠፋብኝ ዉሉ
ለካስ አንቺ ነበርሽ ህይወቴ በሙሉ
ላይ ላዩን እየዋየ ዉስጡ እየታየ
ላይ ላዩን እየዋየ ዉስጡ እየታየ ወይ ልቤ ጉዱ ታየ
ሀዬ በል ሀዬ ሀዬ ሀዬ በል ሀዬ
ሀዬ በል ሀዬ ሀዬ ሀዬ በል ሀዬ ወይ ልቤ ጉድህ ታየ
የፍቅርሽ ጉልበት ሲለካ
በምንም አይተካ
ልቤ ከንቱ ሲመካ
ጥሎታል ፍቅርሽ ለካ
ልቤ ሲመዘን ሲለካ
በፍቅርሽ ወድቋል ለካ
ማመን እንጂ ሲነቃ
መሸፋፈኑ በቃ
ታወቀብኝ ተነቃ ተነቃ
ያላንቺ አልኖርም በቃ
ታወቀብኝ ተነቃ ተነቃ
ያላንቺ አልኖርም በቃ
ከማጀትም አልፎ አደባባይ ወቷል
ፍቅሬን ፀሀይ ሞቆት ሰዉ ሁሉ ሰምቶታል
እዘልቀዉም እና ከእንጊዲህ ደብቄ
የያዘኝን ፍቅር ልያዘዉ አጥብቄ
ላይ ላዩን እየዋየ ዉስጡ እየታየ
ላይ ላዩን እየዋየ ዉስጡ እየታየ ወይ ልቤ ጉዱ ታየ
ሀዬ በል ሀዬ ሀዬ ሀዬ በል ሀዬ
ሀዬ በል ሀዬ ሀዬ ሀዬ በል ሀዬ ተነቃብህ ፀሃዬ
ላይ ላዩን እየዋየ ዉስጡ እየታየ
ላይ ላዩን እየዋየ ዉስጡ እየታየ ወይ ልቤ ጉዱ ታየ
ሀዬ በል ሀዬ ሀዬ ሀዬ በል ሀዬ
ሀዬ በል ሀዬ ሀዬ ሀዬ በል ሀዬ ወይ ልቤ ጉድህ ታየ
ሀዬ በል ሀዬ ሀዬ ሀዬ በል ሀዬ
ሀዬ በል ሀዬ ሀዬ ሀዬ በል ሀዬ ተነቃብህ ፀሃዬ



Credits
Writer(s): Elias Woldemariam, Moges Teka
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link