Yenieta

የያሬድን ዜማ ዝማሬ ቅኝት
ያንን መነሻዬን ፊደሌን መልዕክት ፊደሌን መልዕክት
የቆሎ ተማሪ ያንን ልጅነት
አሁን ትዉስ አሉኝ ታዩኝ መሪጌታ መምህሬ
አሀዱ መነሻ የእዉቀት ጅምሬ
ታየኝ ልጅነቴ የጠርሙሱ ቆሎ ከፊደል ገበታ
እዉቀት የመገቡኝ የኔታ
ከ ሀ ካአቦጊዳ መልዕክቴ (ፊደሌ)
ነፍሴን ሊያስታርቋት አባቴ (ፊደሌ)
ከአለም ከብራናዉ አግባቡኝ (ፊደሌ)
ከእዉቀት መናቸዉም መገቡኝ (ፊደሌ)
አቤት የፊደሉ ገበታ (ፊደሌ)
አቤት የልጅነት ትዝታ (ፊደሌ)
መጣ ድቅን አለ ከፊቴ (ፊደሌ)
እዉቀት የመገቡኝ የኔታ (ፊደሌ)
ሀ ልበል እስኪ ሀሁ ሀ ልበል እስኪ ሀሁ
ጠርሙዜን ቆሎ ሞልቼ (ሀ ሀሁ)
ፊደሌን ከጉያዬ ከትቼ (ሀ ሀሁ)
ድንጋይ ላይ ያስተማሩኝ የኔታ (ሀ ሀሁ)
አይጠፋም መምህሬ ሁኔታ (ሀ ሀሁ)
ሀ ሁ ሂ ሀ ሄ ህ ሆ (ሀ ሀሁ)
ፊደሉን ሳያቸዉ መልሰዉ ያዪኛል
ሌላዉ ሲያነባቸዉ እኔን ይጨንቀኛል
የዘመድ ሰላምታ ሲመጣ ደብዳቤ
መርዶ እየመሰለኝ ሲደነግጥ ልቤ
ማንበብና መፃፍ ዋናዉ ቁምነገር
ከህይወቴ ጐሎ እሸበር ነበር
ማንበብና መፃፍ ዋናዉ ቁምነገር
ከህይወቴ ጐሎ እሸበር ነበር
ሀ ሀሁ ሀ ሀሁ ሀ ሀሁ ሀ ሀሁ
የያሬድን ዜማ ዝማሬ ቅኝት
ያንን መነሻዬን ፊደሌን መልዕክት ፊደሌን መልዕክት
የቆሎ ተማሪ ያንን ልጅነት
አሁን ትዉስ አሉኝ ታዩኝ መሪጌታ መምህሬ
አሀዱ መነሻ የእዉቀት ጅምሬ
ታየኝ ልጅነቴ የጠርሙሱ ቆሎ ከፊደል ገበታ
እዉቀት የመገቡኝ የኔታ
አሁን ማን ወሰደዉ ፊደሌን (ፊደሌ)
አሁን ማን ወሰደዉ ፊደሌን (ፊደሌ)
የእዉቀት ገበታዬን መማሪያ (ፊደሌ)
ሀገር ዕዝ መልእክቴን ማደሪያ (ፊደሌ)
አቤት የፊደሉ ገበታ (ፊደሌ)
አቤት የልጅነት ትዝታ (ፊደሌ)
መጣ ድቅን አለ ከፊቴ (ፊደሌ)
እዉቀት የመገቡኝ የኔታ (ፊደሌ)
ሀ ልበል እስኪ ሀሁ
ሀ ልበል እስኪ ሀሁ
ጠርሙዜን ቆሎ ሞልቼ (ሀ ሀሁ)
ፊደሌን ከጉያዬ ከትቼ (ሀ ሀሁ)
ድንጋይ ላይ ያስተማሩኝ የኔታ (ሀ ሀሁ)
አይጠፋም የመምህሬ ሁኔታ (ሀ ሀሁ)
ሀ የጠርሙሱ ቆሎ ከፊደል ገበታ እዉቀት የመገቡኝ የኔታ
ፊደል ያስቆጠሩኝ የኔታ የኔ ባለዉለታ (ሀ ሀሁ)
ሀ ትዝ አለኝ ናፈቀኝ ጣፋጭ ልጅነቴ
ድንጋይ ላይ ጥላ ስር ቄስ ትምህርት ቤቴ
ድንጋይ ጥላ ስር ፊደል ስንቆጥር ከየኔታ እግር ስር
ድንጋይ ጥላ ስር እንዲህ ነበር ያኔ ፊደል ስንቆጥር
ድንጋይ ጥላ ስር ፊደል ስንቆጥር ከየኔታ እግር ስር
ድንጋይ ጥላ ስር እንዲህ ነበር ያኔ ፊደል ስንቆጥር
ድንጋይ ጥላ ስር ፊደል ስንቆጥር ከየኔታ እግር ስር



Credits
Writer(s): Elias Woldemariam, Mekonen Lemma
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link