Gelemele

እገሌ አትርፎ እገሌ ከስሯል
እገሌ ቀልቶ እገሌ ጠቁሯል
ስለ ሠው ብቻ ሲሆን ወሬያችን
በጣም አስፈራኝ የኛ ፍቅራችን
እንደነ እንትና አልኖርም እንደነ እገሌ
እንደራሴ ነው ምኖረው ልክ እንደ ዐመሌ
እንደነ እንትና አልኖርም እንደነ እገሌ
ስለ ፍቅራችን ስትይ ተይ ገለመሌ
እንቶ ፈንቶና ወሬ ገለመሌ
ተይ አይጠቅመንም ፍቅሬ ገለመሌ
ስለ ሰው ስናወራ ተይ ተይ ፍቅሬ
የኛን ነገር አደራ ተይ ተይ ፍቅሬ
እንደነ እንትና አልኖርም እንደነ እገሌ
እንደራሴ ነው ምኖረው ልክ እንደ ዐመሌ
እንደነ እንትና አልኖርም እንደነ እገሌ
ስለ ፍቅራችን ስትይ ተይ ገለመሌ
እገሌ አልቅሷል አልቅስ አትበይኝ
እገሌ ስቋል ሳቅ አትበይኝ
የራሴ እምባ አለኝ የራሴ ሳቅ
ሰው ተከትዬ አልሳቀቅ
እንደነ እንትና አልኖርም እንደነ እገሌ
እንደራሴ ነው ምኖረው ልክ እንደ ዐመሌ
እንደነ እንትና አልኖርም እንደነ እገሌ
ስለ ፍቅራችን ስትይ ተይ ገለመሌ
ከሰው ጋ መፎካከር ገለመሌ
ከሰው ጋ መወዳደር ገለመሌ
እስቲ ስለኛ እናውራ ነይ ነይ ፍቅሬ
በግልፅ እንመካከር ነይ ነይ ፍቅሬ
እንደነ እንትና አልኖርም እንደነ እገሌ
እንደራሴ ነው ምኖረው ልክ እንደ ዐመሌ
እንደነ እንትና አልኖርም እንደነ እገሌ
ስለ ፍቅራችን ስትይ ተይ ገለመሌ
ሰው እንደቤቱ ይኖራል እንጂ
እንደ ጎረቤትማ መቼም አይበጅ
ለመመሳሰል ከመሰባሰብ
በስንት ጣዕሙ ፍቅሬ ለብቻ ማሰብ
እንደነ እንትና አልኖርም እንደነ እገሌ
እንደራሴ ነው ምኖረው ልክ እንደ ዐመሌ
እንደነ እንትና አልኖርም እንደነ እገሌ
ስለ ፍቅራችን ስትይ ተይ ገለመሌ



Credits
Writer(s): Abdu Kiar Kahssay
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link