Papapa

የጥንት የጠዋቱን ፍቅራችንን ረስተሽ
ባንድ ሰሞን ሆታ ፍቅሬ ተለውጠሽ
ሰማይ ልኑር አልሽኝ አፈር ቤቴን ጠልተሽ
እነቶሎቶሎን እነአዳንቄን ሰምተሽ
እነቶሎቶሎ ምናቸው ይሰማል
ከፈረሱ በፊት ጋሪያቸው ይቀድማል
ከ ሀ እንደመጀመር ውሉን እየረሱ
ፐ ብለው ጀምረው ቤቴን አፈረሱ
ፓፓፓ ፓፓፓ ፓፓፓ ፓፓፓ
ፓ ፓ ፓ ቀየረሽ ወይ ፓፓፓ ይሄ ከንቱ ውዳሴ ፓፓፓ
ምናለ ቀስ ብትይ ፓፓፓ ብትረጋጊ ነፍሴ ፓፓፓ
ፓፓፓ ፓፓፓ ፓፓፓ ፓፓፓ
ይጣፍጥሽ ይሆናል ፓፓፓ መደነቅ መከበብ ፓፓፓ
ነገ መኖሩን እንጃ ፓፓፓ የዛሬ አጀብ አጀብ ፓፓፓ
አዘንኩልሽ እንጂ አልተቀየምኩሽም
የነአዳንቄ ነገር ምንም አልገባሽም
ዛሬ ያሞግሱና ያንቆላጵሱና
ነገ ይዘልፉሻል ይገለበጡና
ከጥንት ጀምሮ ስንበረብረው
ጌሾ ብቻ አይደለም አንጎል የሚያዞረው
ጭብጨባም ሲበዛ በጣም ነው ሚያሰክረው
ፍቅሬ ረጋ ብለሽ ሁሉን እንመርምረው
ፓፓፓ ፓፓፓ ፓፓፓ ፓፓፓ
ፓ ፓ ፓ ቀየረሽ ወይ ፓፓፓ ይሄ ከንቱ ውዳሴ ፓፓፓ
ምነው ባንዴ ረሳሽው ፓፓፓ የፍቅራችንን ጊዜ ፓፓፓ
ፓፓፓ ፓፓፓ ፓፓፓ ፓፓፓ
ይጣፍጥሽ ይሆናል ፓፓፓ መደነቅ መከበብ ፓፓፓ
ነገ መኖሩን እንጃ ፓፓፓ የዛሬ አጀብ አጀብ ፓፓፓ
አጀብ አጀብ አጀብ አጀብ
የኛ ፍቅር ፈረሰ ስምሽ ሲካብ
አጀብ አጀብ ጉድ አጃይባ
ስንቱን ለያይቶ ይሆን ይሄ ፓ ፓ ፓ
አጀብ አጀብ ወይ ያጀብ ጣጣ
ወዳጅ ይተዋል እንዴ ዝና ሲመጣ
አጀብ አጀብ ከንቱ ሙገሳ
ልብሽ ምነው ታበየ ያለፈን ረሳ



Credits
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link