Boobooye

ባወቅኩሽ በቀረብኩሽ ቁጥር
አዛኝ ነሽ ሆደ ቡቡ ፍቅር
የሚገርም ጥሩ ልብ ስላለሽ
አፍቅሮ ልቤ ተከተለሽ

ቡቡዬ ብታምኚም ባታምኚም
ያላንቺ እኔ አይሆንልኝም

ውበትሽ ሲገርመኝ ፀባይና አመልሽ ልቤን ገዝቶታል
ከእማዬ በኋላ እንዳንቺ የሚያዝንልኝ ፍጡር የታል
ዘመኑ ከተማው ኑሮው ጥሎ ማለፍ በሆነበት
ዕድል ነው መባረክ እንዳንቺ አይነት ምቹ ፍቅር ማግኘት
አለ ከሚባለው ከዚች ዓለም ተድላ
ሚኖር አይመስለኝም ለኔ ካንቺ ሌላ
አለ ከሚባለው ከዚች ዓለም ደስታ
ሚኖር አይመስለኝም ለኔ ባንቺ ቦታ

ቡቡዬ ብታምኚም ባታምኚም
ያላንቺ እኔ አይሆንልኝም
ቡቡዬ ውሸት ምን ያደርጋል
ያላንቺ ሌቱስ መች ይነጋል

ባወቅኩሽ በቀረብኩሽ ቁጥር
አዛኝ ነሽ ሆደ ቡቡ ፍቅር
የሚገርም ጥሩ ልብ ስላለሽ
አፍቅሮ ልቤ ተከተለሽ

ቡቡዬ ብታምኚም ባታምኚም
ያላንቺ እኔ አይሆንልኝም

ሲጨንቀኝ ስከፋ እንድበረታና እንድፀና
የሚያረገኝ ፍቅርሽ ነው እመሰክራለሁ ያንቺን ሚና
በክፉም በደጉም እመኚኝ ከጎንሽ እሆናለሁ
ዘላለም አለሜን ስወድሽ ሳፈቅርሽ እኖራለሁ

አለ ከሚባለው ከዚህ ዓለም በጎነት
ሚኖር አይመስለኝም ያንቺ አይነት ደግነት
ውድ ነሽ ቡቡዬ ካንጀት የምትራሪ
እንደኔ ማናለ የታደለ አፍቃሪ
ቡቡዬ ብታምኚም ባታምኚም
ያላንቺ እኔ አይሆንልኝም
ቡቡዬ ውሸት ምን ያደርጋል
ያላንቺ ሌቱስ መች ይነጋል
ያላንቺ
ሌቱስ መች ይነጋል ያላንቺ



Credits
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link