Zimitayie

ዝምታዬ
ድርሻዬ ነው ፋንታዬ
ልኬ ነው በቃ አያምረኝም ስሞታ
ምልልሱ አያምርብኝ
እነሱን መሆን እንዳይሆብኝ
የተባለውን ችዬ ይሁና ብዬ
አለሁ ዝም ብዬ

ዝምታዬ
ድርሻዬ ነው ፋንታዬ
ልኬ ነው በቃ አያምረኝም ስሞታ
ምልልሱ አያምርብኝ
እነሱን መሆን እንዳይሆብኝ
የተባለውን ችዬ ይሁና ብዬ
አለሁ ዝም ብዬ

መልስ የለኝ ሁሌም ለነገር
ተግባባሁ ባለመናገር
ምላስም ምላሽም የለኝ
ባርምሞ ማለፍ ቀለለኝ

ያለስሜ ተሠይሜ
እንደሰማሁ ተገርሜ
ያንደበቴ በር ከርችሜ
ዝም እላለሁ ደጋግሜ

መልስ የለኝ ሁሌም ለነገር
ተግባባሁ ባለመናገር
ምላስም ምላሽም የለኝ
ባርምሞ ማለፍ ቀለለኝ

ያለስሜ ተሠይሜ
እንደሰማሁ ተገርሜ
ያንደበቴ በር ከርችሜ
ዝም እላለሁ ደጋግሜ

ዝምታዬ
ድርሻዬ ነው ፋንታዬ
ልኬ ነው በቃ አያምረኝም ስሞታ
ምልልሱ አያምርብኝ
እነሱን መሆን እንዳይሆንብኝ
የተባለውን ችዬ ይሁና ብዬ
አለሁ ዝም ብዬ

አፍ ያለው ያሻውን ቢልም
ከፀጉሬ አንዲት አትጎልም
ላይጠቅመኝ አልታገልም
አልወቅር ሰውም አልጥልም

ያለስሜ ተሠይሜ
እንደሰማሁ ተገርሜ
ያንደበቴ በር ከርችሜ
ዝም እላለሁ ደጋግሜ

ያለስሜ ተሠይሜ
እንደሰማሁ ተገርሜ
ያንደበቴ በር ከርችሜ
ዝም እላለሁ ደጋግሜ

ያለስሜ ተሠይሜ
እንደሰማሁ ተገርሜ
ያንደበቴ በር ከርችሜ
ዝም እላለሁ ደጋግሜ

ያለስሜ ተሠይሜ
እንደሰማሁ ተገርሜ
ያንደበቴ በር ከርችሜ
ዝም እላለሁ ደጋግሜ



Credits
Writer(s): Bewketu Seyoum
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link