Yemiwedlat

እሷ አትኮራም እንጂ ባላት ዉበት
ብትኮራም ማንም ሰዉ አይፈርድባቴ
እንኳን ጨዋታዋ
እንኳን ፈገግታዋ
ያምራል ዝምታዋ
ለኔስ ብዙ አላት
ብዙ ብዙ አላት
የምወድላት

እናንተ ዝም በሉ እሷ ትሳቅ ታዉራ
ያንሳታል ለሷስ በተራ
አካለ ሴሉን ታንቃዉ እንደወፍ ዘምራ
ይገርማል የሱ እጅ ስራ
እንኳን ተኳኩላ እንኳን ተቀባብታ
ያንሳታል ለሷስ በተራ
አይ ታምራለች ስትታይ በጠዋት ተነስታ
ይገርማል የሱ እጅ ስራ

አቤት አይኗን ስወድላት
እይዋትማ ቆንጆ እኮ ናት
ምንም የለም የሚጐላት
እንዴት አርጎ አሳመራት
አቤት አይኗን ስወድላት
እይዋትማ ቆንጆ እኮ ናት
ምንም የለም የሚጐላት
እንዴት አርጎ አሳመራት

እሷ አትኮራም እንጂ ባላት ዉበት
ብትኮራም ማንም ሰዉ አይፈርድባት
እንኳን ጨዋታዋ
እንኳን ፈገግታዋ
ያምራል ዝምታዋ
ለኔስ ብዙ አላት
ብዙ ብዙ አላት
የምወድላት

ከሰዉ የተለየ አሳመራትና
ያንሳታል ለሷስ በተራ
እያደር ድንቅ አረጋት አላያትም ፈተና
ይገርማል የሱ እጅ ስራ
እንዴት አገኘሃት አትበሉኝ አደራ
ያንሳታል ለሷስ በተራ
የራሴ ሆናለች ለራሴዉ ተፈጥራ
ይገርማል የሱ እጅ ስራ

አቤት አይኗን ስወድላት
እይዋትማ ቆንጆ እኮ ናት
ምንም የለም የሚጐላት
እንዴት አርጎ አሳመራት
አቤት አይኗን ስወድላት
እይዋትማ ቆንጆ እኮ ናት
ምንም የለም የሚጐላት
እንዴት አርጎ አሳመራት

አቤት አይኗን ስወድላት
እይዋትማ ቆንጆ እኮ ናት
ምንም የለም የሚጐላት
እንዴት አርጎ አሳመራት



Credits
Writer(s): Meselle Getahun
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link