Eyerusalem

አምላክ ሰውን ሰራ መልኩን ፈለገና
አብሮት እንዲኖር ፍቅር ያዘውና
የሰው ልጅ አመፀ ልቡን አደንድኖ
አውቆ እንዳልሰማ ጆሮ ዳባ ብሎ

የአምላክ ዓላማ ሰውን ሲፈጥር
ምድርን ገዝቶ እንዲኖር
አትንካ ያለውን ፍሬን ሲበሉ
ባለመታዘዝ ከእርሱ ተጣሉ
ኢየሩሳሌም ፥ ኢየሩሳሌም ሆይ

ፍቅር ግድ አለው ሞቶ ሊያድናት
መጥቶ ሊወስዳት አጭቷት ሄደ
እንድትዘጋጅ ጊዜ ቢሰጣት
ውበቷ ጠፋ ይባስ ተካደ
ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ

አዝ፦ ኢየሩሳሌም ሆይ (ኢየሩሳሌም፡ ሆይ)
ኢየሩሳሌም ሆይ
ኢየሩሳሌም ሆይ (ኢየሩሳሌም፡ ሆይ)

የሃይማኖት ቤት አንቺን ለሚያይ
ወገኛ ግብዝ ፈሪሳዊ
በአንደበትሽ ታከብሪዋለሽ
ልብሽ እርቆ አንቺ አስመሳይ
ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ

አንድ አካል አርጐ ሰርቶሽ ነበረ
ጐራ ለይተሽ ፈራርሰሽ
የቀድሞ መልክሽ ውበትሽ የለም
ተይ ተመለሺ ሳይለይሽ
ኢየሩሳሌም ፥ ኢየሩሳሌም ሆይ

አዝ፦ ኢየሩሳሌም ሆይ (ኢየሩሳሌም፡ ሆይ)
ኢየሩሳሌም ሆይ
ኢየሩሳሌም ሆይ (ኢየሩሳሌም፡ ሆይ)

አምላክ አለቀሰ ተረሳሁኝ ብሎ
ጅራፉን አነሳ ቤቱ ተመሳቅሎ
መች እንዲህ አበጀሽ ተለውጧል መልክሽ
ቀናተኛ ነው ጌታ ሌላ ያሰኘሽ ለታ

እወድሽ የለም ወይ ሙሽራዬ ሆይ
ተውበሽ ጠብቂኝ መጽዳትሽን ልይ
መጥቼ እንደወስድሽ ወደኔ ተመለሺ
እኔ ቅዱስ ነኝና ተነሽ ደሜን እዪና

የት ነው ያለሽው (ሙሽራይቱ)
ናፍቆሻል እርሱ (ሙሽራይቱ)
በይ ተዘጋጂ (ሙሽራይቱ)
ደርሷል ሰዓቱ (ሙሽራይቱ)
ነቅተሽ ጠብቂው (ሙሽራይቱ)
በንጹህ ሕይወት (ሙሽራይቱ)
የአንቺ ትጉነት (ሙሽራይቱ)
የእርሱ ፍጥነት (ሙሽራይቱ)

ምፅአቱ ቀርቧልና



Credits
Writer(s): Simone Tsegay
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link