Yimetal

እንዴት እንሆን ይሆን ፊት ለፊት ስናየው
ያዘጋጀነውን ጥያቄ ትተነው
ፈዘን በውበቱ በሚያስደንቅ ግርማው
ዓይን ዓይኑን እያየን እሱን ማወደስ ነው

ይመጣል በግርማው ይመጣል በክብር
ሊወስደን እንድንኖር ከሱ ጋር
ተስፋችን ኢየሱስ በኃይል ይገለጣል
የወጉትም ደግሞ በዓይናቸውን ያዩታል
የሱ የሆኑትን ግን ሊወስድ ይመጣል

ማደሪያው ከኛ ጋር ነው እግዚአብሔር ራሱ
ህመም ወይም ሀዘን በዚያ አይሰማም
እንባችን በሙሉ ታብሶ ከዓይናችን
ከኢየሱስ ጋር ልንኖር አብረን እንሄዳለን

ይመጣል በግርማው ይመጣል በክብር
ሊወስደን እንድንኖር ከሱ ጋር
ተስፋችን ኢየሱስ በኃይል ይገለጣል
የወጉትም ደግሞ በዓይናቸው ያዩታል
የሱ የሆኑትን ግን ሊወስድ ይመጣል

አዲሷ ኢየሩሳሌም ውበቷ የከተማው
የእግዚአብሔር ክብርና በጉ ብርሃኗ ነው
ፀሐይ ወይም ጨረቃ ከቶ አያስፈልግም
የአምላኬ መገኘት ያበራዋል ሁሉንም

እንሄዳለን በክብር
ልንኖር ከሱ ጋር
ይመጣል በክብር
ልንኖር ከሱ ጋር



Credits
Writer(s): Samuel Alemu, Dawit Getachew
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link