አሁንም አሁንም (Bonus)

አሁነም አሁንም ስምክን እጠራለው
እስክትመጣ ድረስ ናፍቆት ሊገለኝ ነው
አሁነም አሁንም ስምክን እጠራለው
እስክትመጣ ድረስ ናፍቆት ሊገለኝ ነው

እስኪ ልናገረው አውጥቼ
ብቻዬን እንደዚ እስከመቼ
እዚ መምጣትህን ሰምቼ
እኔም እፎይ ልበል አጊንቼ
ተራርቆ ፍቅር ይከብዳል
ያንተን ባላቅ ለእኔ ግን ያማል
ልቤ ስንቱን ክፉ ያስባል
ሌላ አይቷል ብሎ ይሰጋል
ከዚ ሁሉ ሃሳብ አድነኝ
ይሄንን ቅዥቴን አስረሳኝ

አሁነም አሁንም ስምክን እጠራለው
እስክትመጣ ድረስ ናፍቆት ሊገለኝ ነው
አሁነም አሁንም ስምክን እጠራለው
እስክትመጣ ድረስ ናፍቆት ሊገለኝ ነው

አህ
የት ነው ያልሽው ጥሪኝ እኔ አመጣለው
ከጎኔ ሁኚና ትንፋሽሽን ልሙቀው
እጆቼን ያዢ አይኖችሽን ልያቸው
ስትጠሪኝ ድምፅሽን ልስማው
ልቀርብሽ ልይዝሽ የኔ ላደርግሽ
ላክፍሽ ልስምሽ ልቤን ልሰጥሽ
ላሳይሽ የውስጤን እፈልጋለው
አንቺ ልጅ ስምሽን ሁሌ እጠራለው
ደግሞ
እገፋለው ተራራውን እኔ አንቺን ላይ
ላገኝሽ እሻለው ሁሌ ሳትጠልቅ ፅሐይ
ላወጋሽ ላሳይሽ የልቤንም
ጨርሶ አትፍሪ ካንቺ ሌላ ከቶ አልልም
ወዳንቺ ልደርስ ሁሌ እኔ እሮጣለው
ዛሬ ቢመሽም ነገ መች እቆማለው
ስትጠሪው ስሜን መስማት እፈልጋለው
ላንቺ ካልሆነ ለማ እተኛለው

አሁነም አሁንም ስምክን እጠራለው
እስክትመጣ ድረስ ናፍቆት ሊገለኝ ነው
አሁነም አሁንም ስምክን እጠራለው
እስክትመጣ ድረስ ናፍቆት ሊገለኝ ነው

አሁነም አሁንም ስምክን እጠራለው
እስክትመጣ ድረስ ናፍቆት ሊገለኝ ነው
አሁነም አሁንም ስምክን እጠራለው
እስክትመጣ ድረስ ናፍቆት ሊገለኝ ነው



Credits
Writer(s): Yared Alemayehu
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link