ለበጎ ነው

ያለፈው አይመለስም
ላጣነው ነፍስ ይማር
ምንም እንኳ ስንስቅ
አንድ ላይ ብናምር
አለቀስኩኝ ብቻዬን
ጎኔ አንተ ሳትኖር
አለቀስኩኝ ብቻዬን
ጎኔ አንተ ባትኖር
ዛሬ ላይ
ነገስ ቢሆን ማን ሊያነቃክ
አሁን ላይ ምኞቴ ከዚህ ቅዠት እንድነቃ
ከእንግዲህ ፀሎቴ ከዚህ በላይ እንዳላጣ
ከእንግዲህ ምኞቴ ከዚህ በላይ እንዳላጣ
ዛሬ ከፋኝ

አለው በለኝ ናፍቄአለው
ድምፅህን ልስማው እንድታፅናናኝ እፈልጋለው
ከጎኔ የለህም ሀዘኔ ነክ ምን ዋጋ አለው
መሄድክ ህመሜ ዝምታክም ለቅሶዬ ነው
ጠይቄአለው መልስ እሻለው
በሟሙት አይኖቼ ሰላምታህን እጠብቃለው
ለበጎ ይሆናል ብዬ ማሰብ እፈልጋለው
ለበጎ ይሆናል ብዬ ማመንን ሽቻለው

ለበጎ ነው
ለበጎ ነው አው
ለበጎ ነው
ለበጎ ነው አው አው

ለበጎ ነው
ለበጎ ነው አው
ለበጎ ነው
ለበጎ ነው አው አው

ያለፈው አይመለስም ላጣነው ነፍስ ይማር
ምንም እንኳ ስንስቅ አንድ ላይ ብናምር
አለቀስኩኝ ብቻዬን ጎኔ አንተ ሳትኖር
አለቀስኩኝ ብቻዬን ጎኔ አንተ ባትኖር
ዛሬ ላይ
ነገስ ቢሆን ማን ሊያነቃክ
አሁን ላይ ምኞቴ ከዚህ ቅዠት እንድነቃ
ከእንግዲህ ፀሎቴ ከዚህ በላይ እንዳላጣ
ከእንግዲህ ምኞቴ ከዚህ በላይ እንዳላጣ
ዛሬ ከፋኝ

ለበጎ ነው ሚያልፍ ማዕበል ቢመታኝ
ለበጎ ነው ሁሌም ቀኑ ቢከዳኝ
ለበጎ ነው የኔ ምለው ቢቀማኝ
መርጫለው ማመን ምንም ቢያደማኝ

ሁሉም አለው ጠባሳ
ማይናገረው ከጓዳ
ጥያቄ ለአምላኬ በረታ
በምወደው ሲመጣ

ያለፈው አይመለስም ላጣነው ነፍስ ይማር
ምንም እንኳ ስንስቅ አንድ ላይ ብናምር
አለቀስኩኝ ብቻዬን ጎኔ አንተ ሳትኖር
አለቀስኩኝ ብቻዬን ጎኔ አንተ ባትኖር
ዛሬ ላይ
ነገስ ቢሆን ማን ሊያነቃክ
አሁን ላይ ምኞቴ ከዚህ ቅዠት እንድነቃ
ከእንግዲህ ፀሎቴ ከዚህ በላይ እንዳላጣ
ከእንግዲህ ምኞቴ ከዚህ በላይ እንዳላጣ
ዛሬ ከፋኝ

ለበጎ ነው
ለበጎ ነው አው
ለበጎ ነው
ለበጎ ነው አው አው

ለበጎ ነው
ለበጎ ነው አው
ለበጎ ነው
ለበጎ ነው አው አው



Credits
Writer(s): Yared Alemayehu
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link