Hilina

አጥቢያ ኮከብ ሆ የንጋት
ብሩህነት ሆ ያደላት
ሳታይ እየታየች እጅግ በጣም ደምቃ
ያለድጋፍ ተጉዋዥ መንገዷን አዉቃ
ቀጥተኛ አይምሮ ብልህ
ያደላት ልቦና ብሩህ
ግራ ቀኝ የማታይ ጨዋ ናት
ፈጣሪ ለምክንያት የሰራት
መወደስ መከበር ያንሳታል
ለአይነት ለምሳሌ ፍጥሯታል
ምንም ያልጐደለዉ ስብእና
አብዝቶ ያደላት ሂሊና
ሂሊና ሂሊና እንደእሷ ሁሉም ቢሆን ቀና
ሂሊና ሂሊና የሚያየዉ ታላቁን ነዉና
ሂሊና ሂሊና ቅንነት በጎነት ነዉና
አጥቢያ ኮከብ ሆ የንጋት
ብሩህነት ሆ ያደላት
ሳታይ እየታየች እጅግ በጣም ደምቃ
ያለድጋፍ ተጉዋዥ መንገዷን አዉቃ
ከበጎነት በቀር ክፋትን
አትመልከች ብሎ ፈትሯት
መንገዷን እራሷ ታዉቃለች
አትቀድቅም ሰዉ ትደግፋለች
ጽልመት በወረሰዉ ለሊት
ድል አድራጊ ኮከብ ንግስት
በጠራራ ፀሀይ ቢያጧት
እንካሁን የት ነበርሽ ያሏት
ሂሊና ሂሊና እንደእሷ ሁሉም ቢሆን ቀና
ሂሊና ሂሊና የሚያየዉ ድብቁን ነዉና
ሂሊና ሂሊና ቅንነት በጎነት ነዉና
ሂሊና ሂሊና እንደእሷ ሁሉም ቢሆን ቀና
ሂሊና ሂሊና የሚያየዉ ድብቁን ነዉና
ሂሊና ሂሊና ቅንነት በጎነት ነዉና



Credits
Writer(s): Elias Woldemariam, Tesfaye Mamo
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link