Lanchima
ይመስገን ይመስገን ይህ አይኔ
ፈገግታሽን አይቶ የኔ አለም ብሩህ ሆነ ቀኔ
ዉበትሽን አይቶ የኔ አለም ዘረፈልኝ ቅኔ
ይመስገን ይመስገን ሀሳቤ
ስለአንቺ ተጠቦ የኔ አለም አደብ ገዛ ቀልቤ
ስለአንቺ ተጨንቆ አለሜ ፍቅር ገባ ልቤ
የዉበትሽ ጮራ ጭጋጉን ጠረገዉ
ቤቴን አደመቀዉ ህልሜን አተለቀዉ
ሙሉ ሴትነትሽ ኩድለቴን ሸፈነዉ
የፍቅርሽ ይዘቱ ህይወቴን ለወጠዉ
በአለም አይገኝም አንቺን የሚመስል
ዴዝዴሞናም ታሪክ ሞናሊዛም ስዕል
አቻ የለሽ አንቺ ሚዛን ምንነቴ
አምላክ የሰራሽ ወስዶ ከአጥንቴ
ላንቺማ መለከት ይነፋ ላንቺማ በይፋ
ላንቺማ ነጋሪት ይመታ ሚስጥር የሚፈታ
ላንቺማ ጨረቃዋ ትዉጣ ላንቺማ አጊጣ
ለአንቺማ ዉበትሽን አይታ ትድመቅ በፈገግታ
ይመስገን ይመስገን ይህ አይኔ
ፈገግታሽን አይቶ የኔ አለም ብሩህ ሆነ ቀኔ
ዉበትሽን አይቶ የኔ አለም ዘረፈልኝ ቅኔ
ይመስገን ይመስገን ሀሳቤ
ስለአንቺ ተጠቦ የኔ አለም አደብ ገዛ ቀልቤ
ስለአንቺ ተጨንቆ አለሜ ፍቅር ገባ ልቤ
እንዳይረግፍ እሻለዉ የዉበትሽ ጤዛ
ለማማር መድመቅሽ እሆናለዉ ቤዛ
በጭንቀት ባይስላት ትላንት ሞናሊዛን
ዛሬ አትደፋም ነበር የዉበት አክሊሏን
ሙሉ ሴትነትሽን ዘዉትር አስባለዉ
ለደስታ ሰላምሽ እንቅልፌን አጣለዉ
እድሜ ፀጋ ሰቶሽ ኑሪ ለአለም አንቺ
እኔ ካህን ሆኜሽ እኖራለሁ ለአንቺ
ላንቺማ መለከት ይነፋ ላንቺማ በይፋ
ላንቺማ ነጋሪት ይመታ ሚስጥር የሚፈታ
ላንቺማ ጨረቃዋ ትዉጣ ላንቺማ አጊጣ
ላንቺማ ዉበትሽን አይታ ትድመቅ በፈገግታ
ላንቺማ መለከት ይነፋ ለአንቺማ በይፋ
ላንቺማ ነጋሪት ይመታ ሚስጥር የሚፈታ
ላንቺማ ጨረቃዋ ትዉጣ ለአንቺማ አጊጣ
ላንቺማ ዉበትሽን አይታ ትድመቅ በፈገግታ
ላንቺማ ላንቺማ አጊጣ
ላንቺማ ትድመቅ በፈገግታ
ፈገግታሽን አይቶ የኔ አለም ብሩህ ሆነ ቀኔ
ዉበትሽን አይቶ የኔ አለም ዘረፈልኝ ቅኔ
ይመስገን ይመስገን ሀሳቤ
ስለአንቺ ተጠቦ የኔ አለም አደብ ገዛ ቀልቤ
ስለአንቺ ተጨንቆ አለሜ ፍቅር ገባ ልቤ
የዉበትሽ ጮራ ጭጋጉን ጠረገዉ
ቤቴን አደመቀዉ ህልሜን አተለቀዉ
ሙሉ ሴትነትሽ ኩድለቴን ሸፈነዉ
የፍቅርሽ ይዘቱ ህይወቴን ለወጠዉ
በአለም አይገኝም አንቺን የሚመስል
ዴዝዴሞናም ታሪክ ሞናሊዛም ስዕል
አቻ የለሽ አንቺ ሚዛን ምንነቴ
አምላክ የሰራሽ ወስዶ ከአጥንቴ
ላንቺማ መለከት ይነፋ ላንቺማ በይፋ
ላንቺማ ነጋሪት ይመታ ሚስጥር የሚፈታ
ላንቺማ ጨረቃዋ ትዉጣ ላንቺማ አጊጣ
ለአንቺማ ዉበትሽን አይታ ትድመቅ በፈገግታ
ይመስገን ይመስገን ይህ አይኔ
ፈገግታሽን አይቶ የኔ አለም ብሩህ ሆነ ቀኔ
ዉበትሽን አይቶ የኔ አለም ዘረፈልኝ ቅኔ
ይመስገን ይመስገን ሀሳቤ
ስለአንቺ ተጠቦ የኔ አለም አደብ ገዛ ቀልቤ
ስለአንቺ ተጨንቆ አለሜ ፍቅር ገባ ልቤ
እንዳይረግፍ እሻለዉ የዉበትሽ ጤዛ
ለማማር መድመቅሽ እሆናለዉ ቤዛ
በጭንቀት ባይስላት ትላንት ሞናሊዛን
ዛሬ አትደፋም ነበር የዉበት አክሊሏን
ሙሉ ሴትነትሽን ዘዉትር አስባለዉ
ለደስታ ሰላምሽ እንቅልፌን አጣለዉ
እድሜ ፀጋ ሰቶሽ ኑሪ ለአለም አንቺ
እኔ ካህን ሆኜሽ እኖራለሁ ለአንቺ
ላንቺማ መለከት ይነፋ ላንቺማ በይፋ
ላንቺማ ነጋሪት ይመታ ሚስጥር የሚፈታ
ላንቺማ ጨረቃዋ ትዉጣ ላንቺማ አጊጣ
ላንቺማ ዉበትሽን አይታ ትድመቅ በፈገግታ
ላንቺማ መለከት ይነፋ ለአንቺማ በይፋ
ላንቺማ ነጋሪት ይመታ ሚስጥር የሚፈታ
ላንቺማ ጨረቃዋ ትዉጣ ለአንቺማ አጊጣ
ላንቺማ ዉበትሽን አይታ ትድመቅ በፈገግታ
ላንቺማ ላንቺማ አጊጣ
ላንቺማ ትድመቅ በፈገግታ
Credits
Writer(s): Elias Woldemariam, Fird Yawikal Nigussie
Lyrics powered by www.musixmatch.com
Link
Other Album Tracks
© 2025 All rights reserved. Rockol.com S.r.l. Website image policy
Rockol
- Rockol only uses images and photos made available for promotional purposes (“for press use”) by record companies, artist managements and p.r. agencies.
- Said images are used to exert a right to report and a finality of the criticism, in a degraded mode compliant to copyright laws, and exclusively inclosed in our own informative content.
- Only non-exclusive images addressed to newspaper use and, in general, copyright-free are accepted.
- Live photos are published when licensed by photographers whose copyright is quoted.
- Rockol is available to pay the right holder a fair fee should a published image’s author be unknown at the time of publishing.
Feedback
Please immediately report the presence of images possibly not compliant with the above cases so as to quickly verify an improper use: where confirmed, we would immediately proceed to their removal.