Na beyignina

በደስታ በሃዘንሽ
እንድሆን ከጎንሽ
ቀንም ሆነ ማታ
በፈልግሽው ቦታ
ና በይኝና ልምጣ በርሬ
ከነመውደዴ ከነፍቅሬ
ምንም ብትፈልጊ
እኔ አለሁ አትስጊ
በሌሊት በጠዋት
ባስፈለግኩሽ ሰዓት
ና በይኝና ልምጣ በርሬ
ከነመውደዴ ከነፍቅሬ

ያማረሽን ነገር የሚያስደስትሽን
ሃሳብ እንዳይገባሽ ንገሪኝ ምርጫሽን
አለ እንክብካቤ ሞልቶልሻል ፍቅር
ላንቺ ካልሆነማ ጊዜም ሃብቱም ይቅር

ካወራሽኝ እሰማሻለሁ
ከደበረሽ አዝናናሻለሁ
ያንቺን ነገር አላውቅም እንጂ ፍቅሬ እኔማ እወድሻለሁ

ና በይኝና ልምጣ በርሬ
ከነመውደዴ ከነፍቅሬ

በደስታ በሃዘንሽ
እንድሆን ከጎንሽ
ቀንም ሆነ ማታ
በፈልግሽው ቦታ
ና በይኝና ልምጣ በርሬ
ከነመውደዴ ከነፍቅሬ
ምንም ብትፈልጊ
እኔ አለሁ አት ስጊ
በሌሊት በጠዋት
ባስፈለግኩሽ ሰዓት
ና በይኝና ልምጣ በርሬ
ከነመውደዴ ከነፍቅሬ

እንኳን ና ብለሽኝ እንኳን ጠርተሽኝ
ጧት ማታ አይደለም ወይ ምትወሰውሽኝ
የዘወትር ሕልሜ አንቺ አይደለሽም ወይ
እደርስልሻለሁ ና ብለሽኝ አልቆይ

ካወራሽኝ እሰማሻለሁ
ከደበረሽ አዝናናሻለሁ
ያንቺን ነገር አላውቅም እንጂ ፍቅሬ እኔማ እወድሻለሁ

ና በይኝና ልምጣ በርሬ
ከነመውደዴ ከነፍቅሬ
Just call me, Just call me and I will be there.
Just call me, Just call me and I will be there.



Credits
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link